Saturday, October 27, 2018


የልዩ ሀይል ድብደባ ቀጥሏል
ዛሬ ጧት ረፋድ ላይ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ወጣቶች በአፋር ብህራዊ ክልላዊ መንድስት ልዩ ሀይል ክፉኛ ተደበደቡ፡፡ እነኝህ ወጣቶች በአገራችን ላይ (በአንዳንድ አከባ) የመጣው ለውጥ ተካፋይ እንሆን ለውጡ እኛንም ይመለከታል በማለት የክልሉ ገጂ ፓርቲን እየተፋጠጠ ያለው ወጣቱ እያነሳ ያለዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ፣ የመሠረተ ልማት ጥያቄ፣ የክልሉን የተፈጥሮ ሀብት የክልሉ መህበረሰብ ይጠቀም ከትግራይ እጅ ይውጣልን፣ በክልሉ ፖለቲካ የትግራይ ካድሬዎች ጣለቃ ገቢነት ይቁም/ይብቃ የሚሉና የመሳሰሉት ስር ነቅል ለውጥ ጥያቄዎችን በማሳማት ላይ ያሉትን ወጣቶችን ግማሹን ለእስር ግማሹን ለከፋ ጉዳት እየዳረገ ያለው የክልሉ ገጂ ፓርቲ ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ-ሰብዓዊ ድርግት እየፈፀመ በመሆኑ የፈደራል መንግስት መላ ልያበጅለት ይገባል፡፡
በሁን ዘመን የዜጋን መብት በረገጣና በአምባገነን ስረዓት መሳጣት ስለ ማይቻል ለክልላችን ብሎም ለኢትጵያችን የሚበጃት የመጣዉን አዲስ የመልካም ለውጥ ንፋስ ለመላው የአገሪቷ ክልሎች ይደርስ ዘንድ ሁሉም ብረባረብ እና አጉል የስልጣን ጥማት ቆርጠን ለውጡን ብንቀዳጅ የተሸለች ኢትዮጵያን እንገነባለን፡፡ ስለሆነም የአፋር ብህራዊ ክልላዊ መንግስት ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆ አስፈላጊዉን ስር ነቀል ለውጥ መድረግና ለወጣቱ እሮሮ ጆሮ ዳባ ከሚል አበት ቢሎ መስተናገድ ቢችል የተሸለ ዉጤት ያመጣል ባይ ነኝ፡፡
በመጨረሻ ህዝብን ከህዝብ፣ ጎሳን ከጎሳ ለማገጨት እየዶሎቱ ያሉት የክልሉ ወንበደዎችና የትግራይ ወሮ በሎች እጃቸዉን ቢሰበሲቡ ለወደፊት እጣ ፈንታቸው የተሸለ መሆኑን መስጠንቀቂያ አዘል አቅጣጫ እያመለከትኩኝ በዚሁ እቋጫለሁ፡፡

 Idris Kardalo
 Abdu Danaba

Sadik Hussen 

No comments:

Post a Comment